@extends('admin/layouts/default')
{{-- Page title --}}
@section('title')
Dashboard
@parent
@stop
{{-- page level styles --}}
@section('header_styles')
@stop
{{-- Page content --}}
@section('content')
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ካፌ መቆጣጠሪያ ሲስተም
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አመራር ፎረም በ2ዐዐ9 ዓ.ም. የአካዳሚክ ዘርፍ የ6 ወራት የለውጥ ተግባራት አፈፃፀም ላይ በአካዳሚክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር በለጠ ያዕቆብ የሱፐርቪዥኑ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጐበታል፡፡
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር እና የአካዳሚክ ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ ዶ/ር በለጠ ያዕቆብ የዩኒቨርሲቲው ኮሌጆች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ተቋማትና የአካዳሚክ ዘርፍ አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች የ6 ወራት የለውጥ ተግባራት አፈፃፀም ዝርዝር ሪፖርት ለፎረሙ አቅርበዋል፡፡ እርሳቸው ባቀረቡት ሪፖርት በየዘርፉ አደረጃጀቶች የተከናወኑ ተግባራት ፣ የመልካም አስተዳደር ስራዎች፣ የተሰጡ የማህበረሰብ አገልግሎቶች፣ የተሰሩ ምርምርና ጥናቶች፣ የተሰጡ የምክር አገልግሎቶችና የተደረጉ ድጋፎች በስፋት ተዳሰዋል፡፡
በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ጠንካራ የመረጃ አያያዝና ልውውጥ መኖር፣ በቴክኖሎጂ ኮሌጅ የአማካሪ መምህራን መመሪያ መዘጋጀቱ፣ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የሚያበረታታ የማህበረሰብ አገልግሎት፣ በመሬት አስተዳደር ተቋም የአማካሪ መምህራን የተማሪዎች የመረጃ አያያዝ፣ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ በማህበረሰብ አገልግሎት በቂ ስልጠና መስጠት፣ በሶሻልና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት መሰጠቱ፣ በህግ ትምህርት ቤት በ7 ማዕከላት የነፃ ህግ አገልግሎት መስጠቱ፤ በህክምና ትምህርት ቤት፤ የተሻለ የኮርስ አደረጃጀትና የአሰለጣጠን ስርዓት መኖሩ፣ በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት በርካታ የምርምር ትልመ ጥናቶች መኖራቸው፤ በቤተ መጽሐፍትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በየ15 ቀናት የቢኤስሲ ግምገማ መካሄዱ፣ በተከታታይ ትምህርት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ሳምንታዊ የስራ ክንውን ግምገማ መደረጉ፣ በሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት የሱፐርቪዥን ስራው በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉ እና በስነ ትምህርትና ስነ ባህሪ ተቋም የአስተዳደር ሰራተኞች ከቢኤስሲ ውል በመነሳት የ15 ቀናት ዕቅድ በግለሰብ ደረጃ ማቀድና መገምገም ሁሉም ዘርፎች የጋራ ሊያደርጓቸው የሚገቡ መልካም ተሞክሮዎች እንደሆኑ ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችን በአግባቡ ያለመተግበር፣ የግብዓት አለመሟላት፣ አማካሪ መምህራን በቂ ድጋፍና ክትትል አለማድረግ እንዲሁም የዕቅድ ክንውን ግምገማ በአግባቡ ያለማድረግ የታዩ ውስንነቶች እንደሆኑ ሪፖርቱ አስቀምጧል፡፡
በተያያዘ ዜና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አያና አባዋ የለውጥ ሰራዊት አፈፃፀም አጭር ግምገማ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው 48 የመምህራን፣ 81 የአስተዳደር ሰራተኞችና 225 የተማሪዎች የልማት ቡድኖች መኖራቸውንና 1138 የመምህራን፣ 1988 የአስተዳደር ሰራተኞችና 1853 የተማሪዎች የ1ለ5 አደረጃጀቶች መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ አቶ አያና በአቀረቡት ሪፖርትም የአደረጃጀቶች ጥንካሬንና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በአካዳሚክስ ዘርፍ የ6ወራት ተግባራት አፈፃፀም እና በለውጥ ሰራዊት ላይ በቀረቡት ሁለቱ ሪፖርቶች ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ እንደገለፁት የለውጥ ስራዎች ዋና ተግባራትን ውጤታማ በሆነ አግባብ ለመስራት የሚያስችሉ መሳሪያዎች ስለሆኑ እነሱን ተጠቅሞ መስራት በአገር ደረጃም ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም የለውጥ መሳሪያዎችን መጠቀምና ጥናትና ምርምር ላይ እየተሰራ ያለው ጥሩ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው ልቆ ሊወጣ የሚችልበትን ለይቶ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው ማህበረሰብ 97.7 ኤፍ ኤም ሬድዮ ማህበረሰቡን ለማስተማር እየተሰራ ያለውን ተግባር አበረታተው ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ዘርፎች የሬድዮ ጣቢያውን ማህበረሰቡን ለማስተማርና የተሰሩ ስራዎችን ለማስተዋወቅ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም የሱፐርቪዥን ዓላማ መደገፍ በመሆኑ ቡድኑ በየዘርፍ የተመለከታቸውን ክፍተቶች ትኩረት ሰጥቶ በመስራትና የተጀመረውን አጠናክሮ በመቀጠል መንፈቅ ዓመቱን በተሻለ አግባብ ለመጨረስ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ዶ/ር ንጉሴ አሳስበዋል፡
--}15
{{-- @lang('button.create')--}}
{{--
@stop
{{-- page level scripts --}}
@section('footer_scripts')
@stop