ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንት /Global Entrepreneurship Week/ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ተግባራት ተከበረ
Posted by Burie Campus · Nov 26, 2026
ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንት /Global Entrepreneurship Week/ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ተግባራት ተከበረ
ዓለም አቀፍ የሥራ ፈጠራ ሳምንትን (Global Entrepreneurship Week) አስመልክቶ፣ ከኅዳር 16 እስከ 22/2026 በሚከበረው ሳምንት ለተመራቂ ተማሪዎች የሥራ ፈጠራ ሥልጠና ወርክሾፕ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።
ሳምንቱ “Entrepreneurs Thrive Here” (እሴት ፈጣሪዎች እዚህ ይበለጽጋሉ) በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን፣ የሥራ ፈጠራ ባህልን ማሳደግ፣ የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ ተግባራዊ የንግድ ሥራ መቀየርና ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክቱ እሴት ፈጣሪዎችን ማበረታታት ዓላማ አድርጎ ተከብሯል።
በሳምንቱ ማጠቃልያ የሰራ ፈጠራ ወርክሾ የተደረገ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማኅበረሰብ ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት መልካሙ በዛብህ (ዶ.ር) በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ዩኒቨርሲቲው የሥራ ፈጠራንና ፈጠራን በማበረታታት የተማሪዎችና የማኅበረሰቡን አቅም ማጎልበት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራን ማስፋፋትና የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ ምርታማነት መቀየር እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።
በወርክሾፑ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲን የሥራ ፈጠራ ጉዞ አስመልክቶ የቅጥርና የሥራ ፈጠራ ልማት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ይበልጣል ታረቀኝ ጽሑፍ አቅርበዋል። እንዲሁም የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንት አንዳርጋቸው ባይሌ (ዶ.ር) “Effective Entrepreneurial Ecosystem” በሚል ርዕስ ጽሑፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።
በተጨማሪም የንግድ ስራ ፈጠራ ስዎችን፣ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተማሪዎች በተሳተፉበት የፓናል ውይይት፣ የሥራ ፈጠራ አስፈላጊነት፣ የንግድ ሀሳብ ማመንጨት፣ የፈጠራ አቅምን ማሳደግና ሀሳቦችን ወደ ተግባራዊ የሥራ ዕድሎች መቀየር በሚመለከት ልምድ ልውውጥና ውይይት ተደርጓል።
በወርክሾፑ መዝጊያ ንግግራቸው የአካዳሚክ ጉዳዮች ልዩ ረዳት ደመቀ ፍስሃ (ዶ.ር)፣ ዩኒቨርሲቲው የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በቅጥር ሥራ ላይ ብቻ ከመመካት ይልቅ የራሳቸውንና የሌሎችን የሥራ ዕድል የሚፈጥሩ እሴት ፈጣሪዎች እንዲሆኑ የሥራ ፈጠራ ወርክሾፖች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ደመቀ ፍስሃ (ዶ.ር) ሳምንቱ በዚህ መልኩ እንዲከበር ጉልህ ሚና ለነበረው ለኢንተርፕርነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ልዩ ምስጋና አቅርበዋል፡፡




